የአዲስ አበባ ባህል ኪነ ጥበብ ቱሪዝም ቢሮ የኪነጥበብ ዘርፍ ምክትል ቢሮ ሃላፊ አቶ ሠርጸ ፍሬስብሐት በበኩላቸው “ለሥነ-ጥበባዊ ሥራዎች ዋጋ የምናሰጠው የጥበብ ባለሙያዎች ዋጋችንን አውቀን አክብረንና አስከብረን መቀጠል ስንችል ነው ብለዋል።”
“የሥዕል ሥራዎችን ልክ በካታሎግ ሰብስቦ የማስቀመጥ ስራ በተያዘው አመት የተሰራ መሆኑ ተገልፆ ለወደፊት ደግሞ የአንጋፋ አርቲስቶችን ሥራ በፅሁፍ አደራጅቶ ለቀጣይ አመት እንዳቀደ ተናግረዋል።” አክለውም የኪነ-ጥበብ ፌስቲቫሉን አቅደው ለስኬቱ ትልቅ ጥረት ላደረጉት ለኪነ-ጥበብ መድረኮችና ኩነቶች ዝግጅት ዳይሬክቶሬት ምስጋና አቅርበዋል።

በመድረኩም ሮያሊቲ የፈጠራ ክፍያ ጥናታዊ ፅሁፍ በአ/ቶ ወሰን ሙሉ ቀርቦ ውይይት ተደርጓል።
አንጋፋው የኪነ-ጥበብ ባለሞያ አብራር አብዶን የሚዘክር ጥናታዊ ፅሁፍ እና ዘጋቢ ፊልም ቀርቦ የእውቅናና ምስጋና ሽልማት ተሰጥቷል ።
ቢሮው የኪነ-ጥበብ ፌስቲቫሉ ሳምንትን አስመልክቶ የላቀ አስተዋፅዎ ላደረጉ አካላት የአዋርድ እና የእውቅና ሰርተፍኬት ሽልማት አበርክቷል።



Leave a Reply